ልግስና ለተቸገሩት

ዴሪክ ፕሪንስ
Published: 1970
Last Updated: Oktober 2026
Read Time: 2
This teaching is not currently available in Bahasa Indonesia.
ለድሆች ቸር መሆን የጽድቅ ሕይወት ማዕከል ሲሆን፣ስስት ግን ወደ ድህነት ይመራል። መዝሙር 112 በጥበብ መስጠትን ከጽናት፣ከክብር እና በእግዚአብሔር ከመታመን ጋር ያገናኘዋል።
ዴሪክ ፕሪንስ ነኝ፤ ከቃሉ ለእናንተ የሚሆን መልዕክት ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ።
ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል። ለዘላለም አይናወጥም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል። ከክፉ ነገር አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው። በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራም። መዝሙር 112:5-7,9
መጽሐፍ ቅዱስ ሁልጊዜ ስለ ልግስና መልካም ነገርን ይናገራል፤ ስለ ንፉግነት ግን የሚናገረው ምንም መልካም ነገር የለም። መጽሐፍ ቅዱስ ጥበብ የተሞላበትና አስተዋይ ልግስና ወደ በረከትና ብልጽግና የሚወስድ መንገድ መሆኑን ያስተምራል፤ ንፉግነት ግን ወደ ድህነት ያመራል።
መዝሙረኛው እዚህ ጋር ጻድቅ ሰውን ይስላል። እንዲህ ይላል፦ “ለዘላለም አይናወጥም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።” ለምን? የዚያ ሰው ጽናት ምክንያቶች ምንድን ናቸው? እርሱ ቸር ነው፣ በልግስና ያበድራል፣ ስጦታዎቹንም በውጪ ለድሆች በትኗል። ስለዚህ ዘማሪው፣ “ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል” ይላል። ዛሬ ብዙዎቻችን ለድሆችና ለተቸገሩ ሰዎች ያለን አመለካከት ለጽድቃችን ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ማስታወስ ያለብን ይመስለኛል። እግዚአብሔር የድሆችን ጩኸትና ፍላጎት ችላ ስለሚሉ ሰዎች የሚናገረው ምንም መልካም ነገር የለም። ይህ ጽድቃችንን ለማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን እናስታውስ።

Unduh Gratis
Renungan ini tersedia untuk diunduh, dicetak, dan dibagikan untuk penggunaan pribadi atau gereja.
Unduh PDFKode: WD-WFTW-087-AMH









