ሁሉን-አቀፍ ግንኙነት

ዴሪክ ፕሪንስ
Published: 1970
Last Updated: Oktober 2026
Read Time: 2
This teaching is not currently available in Deutsch.
የእግዚአብሔር ተስፋ ፈተናዎች የሌለበት ሳይሆን፣በሕይወት ጨለማ ሸለቆዎች ውስጥ የእርሱ አብሮነት ማረጋገጫ ነው። የእርሱ የተግሣጽ በትርና የመጽናኛ ምርኩዝ ለእርሱ ለሚገዙት ተሰጥተዋል፤ይህም በጣም ጥልቅ በሆኑ የፈተና ወቅቶች፤ይህም እጅግ ጨለማ በሆኑ የተግዳሮት ጊዜዎች ውስጥ እንኳን ብርሃንን ያመጣል።
ዴሪክ ፕሪንስ ነኝ፤ ከቃሉ ለእናንተ የሚሆን ቃል ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ። ይህ ቃል የዳዊት መዝሙር ከሆነው ከመዝሙር 23 የተወሰደ ነው። ዳዊት መዝሙሩን እንዲህ በማለት ይጀምራል፦
“እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፤ የሚያሳጣኝም የለም።”
ከዚያም ጌታ እረኛው በመሆኑ ለእርሱ ስለሚሆኑት አቅርቦቶች ሁሉ ይናገራል፤ በቁጥር 4 ላይም እንዲህ ይላል፦
"በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።" (መዝሙር 23:4)
አያችሁ፤እግዚአብሔር ለሕዝቡ በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ እንደማናልፍ ዋስትና አይሰጥም። እንዲያውም፣ መዝሙረኛው በአንድም ሆነ በሌላ ጊዜ በዚያ ውስጥ እንደምናልፍ በእርግጥ ያስባል። ሸለቆው በአካል መሞት ብቻ ነው ብዬ አላምንም። በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ የምናልፍበት በሕይወት ውስጥ ብዙ አጋጣሚዎች አሉ ብዬ አምናለሁ - የሐዘን፣ የብቸኝነት፣የሕመም፣ የድህነት፣ የተስፋ መቁረጥ ጊዜያት። እግዚአብሔር በእነዚያ ሸለቆዎች ውስጥ እንደማናልፍ ቃል አልገባም፤ ነገር ግን ከእኛ ጋር እንደሚሆን ቃል ገብቷል።
በተለይም ደግሞ በትርና ምርኩዙ እንደሚያጽናኑን ቃል ይገባል። ለእኔ በትሩ ተግሣጽን ይወክላል፤ ምርኩዙ ደግሞ መጽናናትን ይወክላል፡፡ የእግዚአብሔርን መጽናናት ከፈለግን ለተግሣጹ መገዛት እንዳለብን አምናለሁ፤ በዚህም መሠረት በጣም ጨለማ በሆነው ሸለቆ ውስጥ እንኳ ስናልፍ ከእኛ ጋር ያለው የእርሱ መገኘት የተረጋገጠ ይሆናል። የእርሱም መገኘት የሸለቆውን ጨለማ ያበራል፡፡

Kostenloser Download
Diese Andacht können Sie herunterladen, ausdrucken und für den persönlichen Gebrauch oder den Gebrauch in der Gemeinde weitergeben.
PDF herunterladenCode: WD-WFTW-027-AMH









