ኃይለኛ ጎርፍ

ዴሪክ ፕሪንስ
Published: 1970
Last Updated: ottobre 2026
Read Time: 2
This teaching is not currently available in Italiano.
በመንፈሳዊ በረሃ ውስጥ ሆናችሁ፤ጌታ ድንገተኛ እና ኃይለኛ የሚያድስ መንፈሱን እንዲያፈስላችሁ እየጸለያችሁ ነውን? ይህ ጸሎት እግዚአብሔር ድርቀታችንን በመንገዳችን ያለውን ማንኛውንም እንቅፋት በኃይል ጠራርጎ ወደሚወስድ ፈጣን ጎርፍ እንዲለውጥ የሚጠይቅ ነው።
ዴሪክ ፕሪንስ ነኝ፤ ከቃሉ ለእናንተ የሚሆን መልዕክት ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ።
አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ። መዝሙር 126:4
የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለ መታደስ የጸለዩት ጸሎት አለ። የኔጌቭን ምድረ በዳ የምታውቁ ከሆነ፣ እዚያ ላይ የተሳለው ምስል በጣም ግልጽ ነው። በአረብኛ “ጅረቶች” ተብሎ የተተረጎመው ቃል “ዋዲ” ይባላል። ዋዲ በዋነኝነት በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኝ ልዩ ነገር ነው። በአመቱ አብዛኛው ጊዜ ደረቅ የሆነ የወንዝ መውርጃ ነው። ውሃ በውስጡ ይፍስ እንደነበር ማየት ይቻላል፤ ነገር ግን ለጥቂት ቀናት ዝናብ ካልዘነበ ይደርቃል፤ ቀድሞ ውሃ ፍሰት እንደነበረው የሚያሳይ ምልክት ብቻ ይቀራል።
ስለዚህ በዚያ ያለው የእግዚአብሔር ሕዝብ በዚያ ጸሎት ውስጥ ራሳቸውን በደቡብ እስራኤል በረሃ በሆኑት በኔጌቭ እንደሚገኙት ደረቅ የወንዝ መውረጃዎች አድርገው ይመለከታሉ። ነገር ግን ጸሎታቸው እግዚአብሔር በኔጌቭ እንዳሉ ፈሳሾች እንዲመልሳቸው ነው። ይህ በጣም ግልጽ የሆነ ምስል ነው፤ ምክንያቱም በኔጌቭ ዝናብ በሚዘንብባቸው በተወሰኑ ወቅቶች ዝናቡ በከፍተኛ ሁኔታ እና በብዛት ስለሚመጣ፣በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ደረቅ የነበረው የወንዝ መውረጃ በፊቱ ያለውን ሁሉ ጠርጎ ወደሚወስድ ኃይለኛ ጎርፍ ይቀየራል፤አንዳንድ ጊዜ ድልድዮችን ጠርጎ ይወስዳል፣አልፎ ተርፎም ከባድ አደጋዎችን ያስከትላል፣መኪኖችንም ጠርጎ ይወስዳል፤ስለዚህም ከጥቂት ሰዓታት በፊት ትቢያ የለበሰ እና ድረቅ ብቻ በነበረበት ቦታ፣ አሁን የሚተምም ኃይለኛ ጎርፍ ይሆናል።
እንግዲህ በመንፈስ የሚያነሳሳ ጸሎታቸውም እግዚአብሔር ሕዝቡን በኔጌቭ ምድረ በዳ እንዳሉ ጅረቶች እንዲያድሳቸው ነው፤ምንም እንኳ የውኃ ምልክት የማይታይብን ደረቅና ትቢያ የለበስን ብንሆንም፣ እግዚአብሔር በድንገት ይጎበኘናል፤ እንቅፋቶችን ሁሉ ጠራርጎ እንደሚወስድ ኃይለኛ ጐርፍ የመንፈሱን ጉብኝት ይልካል።

Scaricare gratuitamente
Questa meditazione può essere scaricata, stampata e condivisa per uso personale o in chiesa.
Scaricare PDFCodice: WD-WFTW-113-AMH









