ለጌታ የተዘጋጀ ስፍራ

ዴሪክ ፕሪንስ
Published: 1970
Last Updated: ottobre 2026
Read Time: 2
This teaching is not currently available in Italiano.
የጌታን መገኘት ለመቀበል በልባችን ውስጥ ለእርሱ ስፍራ ሊኖረን ይገባል። ኩራትና ጥላቻ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ፤ትሕትና ግን አማኞች እግዚአብሔር ሊሰጣቸው የሚፈልገውን እንዲቀበሉ ያዘጋጃቸዋል።
ዴሪክ ፕሪንስ ነኝ፤ ከቃሉ ለእናንተ የሚሆን መልዕክት ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ።
በእውነት ወደ ቤቴ ድንኳን አልገባም፥ ወደ ምንጣፌም አልጋ አልወጣም፥ለዓይኖቼም መኝታ ለሽፋሽፍቶቼም እንቅልፍ፥ ለጕንጮቼም ዕረፍትን አልሰጥም፥ለእግዚአብሔር ስፍራ፥ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ። መዝሙር 132:3-5
እነዚህ ቃላት የተነገሩት በዳዊት የተነገሩ ነው። በፍልስጥኤማውያን ተማርኮ የነበረውን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም የመመለስ አስፈላጊነት ተረድቶ ነበር። ነገር ግን ጌታ በሕዝቡ መካከል የማረፊያ ቦታውን እንዲያደርግ ከመጋበዙ በፊት፣ስፍራ ማዘጋጀት፣ማለትም ስፍራ ፈልጎ ማዘጋጀት እንዳለበት ተገንዝቦ ነበር። በዚህ ውስጥ አንድ ታላቅ መርህ አለ፤ጌታ ከእኛ ጋር እንዲኖር ከመጠየቃችን በፊት ለእርሱ የሚሆን ስፍራ ማዘጋጀት ይኖርብናል።
ጌታ ከእኛ ጋር እንዳያድር የሚከለክሉ ሁለት ታላላቅ እንቅፋቶች እንዳሉ አምናለሁ። ሁለቱም በእንግሊዝኛ ቋንቋ “p” በሚለው ፊደል ይጀምራሉ። የመጀመሪያው ትዕቢት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ጥላቻ ነው። እኛ ትዕቢተኞችና እብሪተኛ እስከሆንን ድረስ ለጌታ የሚሆን ስፍራ አይኖረንም። በገዛ መንገዳችን፣ በገዛ ሀሳባችንና በገዛ አመለካከታችን እስከተጠመድን ድረስ፣ እግዚአብሔር እኛ በሚመስለን መንገድ ብቻ እንዲሰራ እንፈልጋለን ማለት ነው። እነዚህ ሁለት የትዕቢትና የጥላቻ ጋሬጣዎች ጌታ በልባችንና በህይወታችን ውስጥ የማረፊያ ስፍራ እንዳያገኝ ሊከለክሉት ይችላሉ።
ስለዚህ ጌታ የማረፊያ ቦታውን እንዲያደርግ፣በኃይሉ ታቦት እንዲመጣ፣ እንዲሁም የሕልውናውንና የበረከቱን ሙላት ይዞ እንዲመጣ ከመጋበዛችን በፊት፣እግዚአብሔር የሚያርፍበትን ተገቢ የሆነ ቦታ ማዘጋጀታችንን እርግጠኞች መሆን እንዳለብን እናስታውስ።

Scaricare gratuitamente
Questa meditazione può essere scaricata, stampata e condivisa per uso personale o in chiesa.
Scaricare PDFCodice: WD-WFTW-119-AMH









