ዴሪክ ፕሪንስ ነኝ፤ ከቃሉ ለእናንተ የሚሆን መልዕክት ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ።

ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ። መዝሙር 50:14-15

በሕይወታችን ውስጥ በሆነ ወቅት ላይ ሁላችንም መከራ ይገጥመናል። መዝሙረኛው ስለ መከራ ቀን ይናገራል። በሆነ ወቅት ላይ በመከራ ቀን ውስጥ የማያልፍ ከእኛ መካከል አንድም ሰው የለም። ነገር ግን እዚህ መዝሙረኛው ከመከራ የምንወጣበትን መንገድ፣ የደህንነትን መንገድ ይነግረናል። ይህንንም በራሴ ሕይወት ተሞክሮ ብዙ ጊዜ ላረጋግጠው እንደቻልኩ እነግራችኋለሁ።

ከመከራ መውጫው መንገድ ምንድን ነው? "ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ማቅረብ።" በዚያው በመከራህ መካከል ሳላችሁ እምነታችሁን ተለማመዱ እና እግዚአብሔርን ማመስገን ጀምሩ። እርሱን የማመስገንና የማክበርን መሥዋዕት አቅርቡለት። ከዚያም በመከራ ቀን ጥሩት፤ የእርሱም የተስፋ ቃል "አድንሃለሁ" የሚል ነው፤ ይህ ብቻም አይደለም "አንተም ታከብረኛለህ" ይላል። የእግዚአብሔር ማዳን ለክብሩ ይሆናል፤እግዚአብሔር በመከራ ቀን እንዴት እንዳዳነን በሕይወታችን ውስጥ ምስክርነት ይሆናል።

ከዚያም በዚያው የመዝሙረ ዳዊት ክፍል ላይ መዝሙረኛው እንዲህ ይላል፦ “ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።”(ቁጥር 23) ። ስለዚህ፣ በመከራ ውስጥ ስንሆንና ምንም መውጫ መንገድ ባይታየንም እንኳ እግዚአብሔርን ማመስገን ስንጀምርና ያንን የምስጋና መስዋዕት ስናቀርብ፣ እግዚአብሔር ማዳኑን ለእኛ የሚያሳይበትን መንገድ እናዘጋጃለን። እግዚአብሔር የምስጋናን መስዋዕት ለሚያቀርቡለት ሰዎች መንገድን ይከፍታል።

ስለዚህ በመከራ ውስጥ በምትሆኑበት ጊዜ፣መውጫው መንገድ እርሱ መሆኑን አስታውሱ!