ተግባራዊ የሆነ እምነት ማለት ወደ ውጭ መዘርጋት ሲሆን፤ ይህም በዴሪክ ፕሪንስ አገልግሎት የምንናገረውንና የምናደርገውን ሁሉ በትክክል የሚያሳይ ነው።
በዓለም ዙሪያ ያሉ በተለያዩ አገልግሎት ውስጥ የሚነሱ ፍላጎቶችን ወይም ክልሎችን ዓላማ በማድረግ፣የኛ የተልዕኮ አገልግሎቶች በክርስቲያናዊ ደቀ መዝሙርነት ግንባር ቀደም ሆነው ይሠራሉ፤ እንዲሁም አማኞችን ወደ መንፈሳዊ ብስለት እንዲመጡ እንደግፋለን እናም እናስታጥቃለን።
በተግባር ይህ ደቀ መዛሙርትን ደቀ መዛሙርት ለማድረግ የሚያስችል የትምህርት ቁሳቁስ በስፋት መተርጎም፣ ማዘጋጀትና ማሰራጨትን ያካትታል። ሌሎች የተዘረጉ አገልግሎቶች ለችግረኞች ማህበረሰቦችና በእምነታቸው ምክንያት ስደት ለሚደርስባቸው ክርስቲያኖች ድጋፍ መስጠትን ያጠቃልላሉ።
በመላ አገሪቱ የሚገኙ ነዋሪዎችን ለመድረስና ልባቸውን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር የሰጡ አማኞችን ደቀመዛሙርት ለማድረግ ልባዊ ፍላጎታችን ነው። ይህንንም ለማድረግ የዴሪክ ፕሪንስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን የያዙ መጻሕፍት፣ ጽሑፎች፣ የድምጽ ቅጂዎች፣ ቪዲዮዎችና ሌሎችንም ጨምሮ በትርጉም በማዘጋጀትና በማሰራጨት በንቃት እየሠራን ነው። በተሰጠን ምላሽ በእጅጉ ተበረታተናል፤ ሆኖም ግን ብዙ ተጨማሪ እድሎች እንዳሉ ስለምናውቅ በጽናት እንቀጥላለን።
በአካባቢያችን ላለው የወንጌል አገልግሎታችን እንድትጸልዩልንና የገንዘብ ድጋፍ እንድታደርጉልን እንጋብዛችኋለን።
ተግባራዊ የሆነ እምነት ማለት ወደ ውጭ መዘርጋት ሲሆን፤ ይህም በዴሪክ ፕሪንስ አገልግሎት የምንናገረውንና የምናደርገውን ሁሉ በትክክል የሚያሳይ ነው።
በዓለም ዙሪያ ያሉ በተለያዩ አገልግሎት ውስጥ የሚነሱ ፍላጎቶችን ወይም ክልሎችን ዓላማ በማድረግ፣የኛ የተልዕኮ አገልግሎቶች በክርስቲያናዊ ደቀ መዝሙርነት ግንባር ቀደም ሆነው ይሠራሉ፤ እንዲሁም አማኞችን ወደ መንፈሳዊ ብስለት እንዲመጡ እንደግፋለን እናም እናስታጥቃለን።
በተግባር ይህ ደቀ መዛሙርትን ደቀ መዛሙርት ለማድረግ የሚያስችል የትምህርት ቁሳቁስ በስፋት መተርጎም፣ ማዘጋጀትና ማሰራጨትን ያካትታል። ሌሎች የተዘረጉ አገልግሎቶች ለችግረኞች ማህበረሰቦችና በእምነታቸው ምክንያት ስደት ለሚደርስባቸው ክርስቲያኖች ድጋፍ መስጠትን ያጠቃልላሉ።
ከዚህ ጊዜ በላይ ለዚህ አገልግሎት የታየ ፍላጎት ኖሮ አያውቅም።