የሁለት መንግስታት ንጽጽር

ዴሪክ ፕሪንስ
Published: 1970
Last Updated: ሴፕቴምበር 2026
Read Time: 2
የእግዚአብሔር የብርሃንና የፍቅር መንግሥት ከሰይጣን የጨለማ ግዛት በላይ ነው። ዴሪክ ፕሪንስ እነዚህን ሁለት ሥልጣናት በማነጻጸር፣በክርስቶስ ጻድቅ የሆኑ አማኞች ክፋትን መቋቋም እና የተመደበላቸውን ርስት መውረስ እንደሚችሉ ያስተምራል።
ዴሪክ ፕሪንስ ነኝ፤ ከቃሉ ለእናንተ የሚሆን መልዕክት ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ።
"ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የኃጥኣን በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም።" መዝሙር 125:3
ክፋት የስልጣን በትር እንዳለው አስተውላችኋልን? አዎ፣እውነት ነው፤በሰይጣን መንግሥት ውስጥ ሥልጣን አለ። መጽሐፍ ቅዱስ በቆላስይስ 1:12-13 ከጨለማው ግዛት ሥልጣን እንደዳንን እና ወደ እግዚአብሔር የፍቅሩ ልጅ መንግሥት እንደፈለስን ይነግረናል። ፍጹም ተቃራኒ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መንግሥታት አሉ። እነርሱም የጨለማው ሥልጣን መንግሥት እና የብርሃንና የፍቅር መንግሥት የሆነው የእግዚአብሔር የፍቅሩ ልጅ መንግስት ናቸው። እያንዳንዱ መንግሥት ሥልጣን አለው፣ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግስት ሥልጣን በጽንፈ ዓለም ውስጥ ካሉ ከማንኛውም ሥልጣናት ሁሉ በላይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር መንግሥት በሁሉ ላይ ይገዛል፣ለዘላለም የጸና ነው፣ደግሞም የማይናወጥ ነው በማለት ይናገራል።
የእግዚአብሔር መንግሥት አካል ስንሆን፣እግዚአብሔር በእርሱ ስም የጽድቅን በትር እንድንይዝ ይፈቅድልናል፤ይህም በትር የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያለበት ነው። እንግዲህ ይህንን በትር ስንይዝ የክፋትን በትር እንመክታለን፤ እንመታለን፤የክፋትን በትረ ስልጣን እንሰብራለን፣እንዲሁም የሰይጣንን ግዛት እናፈርሳለን። እግዚአብሔርም ለእኛ ወደመደበልን ርስት እንመለሳለን።
ስለዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ በክርስቶስ ያለውን ርስቱን መልሶ እንዲያገኝ የተሰጠ የተስፋ ቃል አለ። “ጻድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ የኃጥኣን በትር በጻድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም” ይላል። ለእናንተም ሆነ ለእኔ በክርስቶስ ባገኘነው ጽድቅ አማካኝነት የተመደበልን ርስት አለ። ያንን በትር በድፍረት መያዝ፣የክፋትንም በትር መምታትና ወደ ተመደበልን ርስት መግባት ይኖርብናል።

ኮድ: WD-WFTW-111-AMH
