የግላዊነት መመሪያ

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ የግል መረጃዎትን ከፍ አድርጎ ያከብራል። ይህ መመሪያ ለማንበብ ቀላል፣ትክክለኛ እና ግልጽነት ያለው እንዲሆን አድርገነዋል፣ ይህም ለግላዊነትዎ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ሲሆን ይህንንም በቁም ነገር እንመለከተዋለን።

ይህ ማስታወቂያ በዚህ ድህረ ገጽ በኩል የተሰበሰበውን መረጃ ሁሉ ይመለከታል።

አጠቃላይ

የግል መረጃ ማለት አንድን ግለሰብ ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል ማንኛውም መረጃ ነው። ለምሳሌ፣ ስምዎ፣ አድራሻዎ፣ የስልክ ቁጥርዎ እና የኢሜል አድራሻዎ የግል መረጃ ሊሆኑ ይችላሉ።

አገልግሎቱ የግል መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በመያዝና በአግባቡ እና በሕግ መሠረት ለማስኬድ የሚያስችሉትን ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎች መውሰድ የአገልግሎቱ መመሪያ ነው። ይህም አገልግሎቱ በሚሰራባቸው አካባቢዎች ካሉት ተገቢ የውሂብ ጥበቃ መርሆዎች እና የግላዊነት ሕጎች ጋር የሚጣጣም ነው።

ሚኒስትሪው ከእርስዎ የሚሰበስባቸው መረጃዎች

ድረ ገፁን ሲጎበኙ፣ ስምዎን፣ የእውቂያ መረጃዎንና ሌሎች ግላዊ መረጃዎችን ጨምሮ የተወሰኑ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ሊጠየቁ ይችላሉ።

አገልግሎቱ ድህረ ገጻችንን እንዴት እንደሚጠቀሙበት መረጃ እንዲሁም ለአገልግሎቱ የሚልኩትን ኢሜይሎች፣ ደብዳቤዎች ወይም የተሞሉ ቅጾች ላይ ያለውን መረጃ ሊሰበስብ ይችላል።

ኩኪዎች

ልክ እንደሚጎበኟቸው አብዛኛዎቹ ድረ-ገጾች፣ የአገልግሎቱ ድረ-ገጽ እርስዎን ለማስታወስ በማስቻል የተጠቃሚ ተሞክሮዎን ለማሻሻል ኩኪዎችን ይጠቀማል። ይህ ለጉብኝትዎ ጊዜ ብቻ ወይም ለወደፊት ጉብኝቶች (ምርጫዎችዎን ለማስታወስ፣ ወዘተ) ሊሆን ይችላል።

ድረ ገጻችን በአግባቡ እንዲሰራ፣ ከገጽ ወደ ገጽ በቀላሉ እንዲዘዋወሩ እና የገቡ ተጠቃሚዎችን እንዲያስታውስ አንዳንድ ኩኪዎች ያስፈልጉታል፤ ለምሳሌ የመግቢያ ዝርዝሮችዎን በማስገባት ወደ ሌላ ገጽ ሲሄዱ፤ድረ ገጹ አስቀድመው መግባታቸውን ኩኪው ስለሚነግረው እንደገና እንዲገቡ አይጠየቁም።

ድህረ ገጻችንን የሚጎበኙ ሰዎችን አይነት ለመተንተን ኩኪዎችን እንጠቀማለን፤ ለምሳሌ የእርስዎ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ የሚጠቀሙበት የአሳሽ ወይም የመሳሪያ (ሞባይል ወዘተ) አይነት፣ እንዲሁም የተመለከቷቸው ገጾች እና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ። ይህ ሁሉ መረጃ የምናቀርበውን አገልግሎት ለማሻሻልና ድህረ ገጻችንን ለእርስዎ ምቹ ለማድረግ ይረዳናል።

እንደ ዩቲዩብ፣ ሳውንድክላውድ ወዘተ ባሉ በገጹ ላይ የተካተቱ ይዘቶችን በሚያስተዳድሩ ውጫዊ ድረ ገጾች አንዳንድ ጊዜ ኩኪዎች ሊቀመጡ ይችላሉ። የእነዚህን ኩኪዎች ስርጭት አንቆጣጠርም። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሶስተኛ ወገን ድረ ገጾችን ማየት ይኖርብዎታል።

ኩኪዎች እንዲቀመጡ ካልፈለጉስ?

በዚህ ወይም በሌላ ድህረ ገጽ የተቀመጡ ኩኪዎችን መገደብ ወይም ማገድ ከፈለጉ፣ ይህንን በአሳሽዎ ቅንብሮች በኩል ማድረግ ይችላሉ። የአሳሽዎ የእገዛ ተግባር እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ያሳየዎታል።

ወይም ደግሞ www.aboutcookies.org የተባለውን ድህረ ገጽ መጎብኘት ትችላላችሁ፤ ይህ ድህረ ገጽ ለተለያዩ አሳሾች (browsers) ይህን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ሰፊ መረጃ የያዘ ነው። ከኮምፒውተርዎ ላይ ኩኪዎችን እንዴት ማጽዳት እንደሚችሉ እንዲሁም ስለ ኩኪዎች አጠቃላይ መረጃ ያገኛሉ።

ይህንን በሞባይል ስልክዎ አሳሽ ላይ እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ ለማወቅ የስልክዎን መመሪያ መመልከት ያስፈልግዎታል።

አገልግሎቱ የግል መረጃዎን እንዴት እንደሚጠቀምበት

አገልግሎቱ የእርስዎን የግል መረጃ ለሚከተሉት ዓላማዎች ሊጠቀምበት ይችላል፡ የድረገፁን አጠቃቀም መከታተልና ማስቻል፣ ሽያጭና ክፍያ፣ ልገሳ መቀበል፣ የአባላትን የመረጃ ቋት ማስተዳደር፣ እንዲሁም ቴክኒካልና ንግድ ነክ ጥናት ማድረግ። ይህንን ድረገፅ በመጠቀም የግል መረጃዎ እንዲህ ጥቅም ላይ እንዲውል ተስማምተዋል።

የሶስተኛ ወገኖች እና የግል መረጃ ይፋ ማድረግ

አገልግሎቱ እንደተገለጸው ዓላማ መሰረት የግል መረጃዎን በእሱ ምትክ እንዲያስተናግዱ ለሚያዟቸው የሶስተኛ ወገኖች ሊያጋራ ይችላል። እነዚህ የሶስተኛ ወገኖች አገልግሎቱ በሚያስቀምጣቸው ዓላማዎች ብቻ የግል መረጃዎን እንዲጠቀሙ እና ያልተፈቀደ ወይም ሕገ-ወጥ መዳረሻን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ በአገልግሎቱ ይጠየቃሉ። ይህንን ድህረ ገጽ በመጠቀም፣ የግል መረጃዎን እንዲህ ባለ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል ተስማምተዋል።

አገልግሎቱ በሚመለከታቸው ሕጎች ወይም ደንቦች መሠረት እንዲያደርግ በሚጠየቅበት ጊዜ የግል መረጃዎን ጨምሮ መረጃዎችን ሊያጋራ ወይም ተደራሽ ሊያደርግ ይችላል።

ውጫዊ አገናኞች

ይህ ማሳሰቢያ ከኛ ውጪ ለሆኑ ድረ-ገጾች አይተገበርም። የምትጎበኟቸውን ድረ-ገጾች የግላዊነት መምሪያዎች እንድታነቡ እንመክራለን።

የGoogle reCAPTCHA (ወይም ተመሳሳይ የሶስተኛ ወገን መሳሪያዎች)

ድረ ገጻችን ደህንነትን ለማጠናከር እና ያልተፈቀደላቸው እንቅስቃሴዎችን ለመከላከል እንደ ጉግል reCAPTCHA ያሉ የሶስተኛ ወገን መሳሪያዎችን ሊጠቀም ይችላል። እነዚህ መሳሪያዎች አንድ ጎብኚ ሰው ወይም አውቶሜትድ ፕሮግራም መሆኑን ለመለየት እንደ የአይ ፒ አድራሻ እና ባህሪ ያሉ ከድረ ገጻችን ጋር ስለሚያደርጉት መስተጋብር መረጃዎችን ሊሰበስቡ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ የእያንዳንዱn ቱል ፕሮቫይደር (Tool provider) የግላዊነት መመሪያ ይመልከቱ።

የግል መረጃዎን ማግኘት፣ ማረም ወይም ማዘመን

አገልግሎቱ ስለእርስዎ የያዘውን የግል መረጃ በጽሑፍ በመጠየቅ ማወቅ ይችላሉ። አገልግሎቱ ለዚህ አገልግሎት ተገቢውን በሕግ የተደነገገውን ክፍያ የመጠየቅ እና አስፈላጊ ከሆነም ተጨማሪ ዝርዝሮችን የመጠየቅ መብት አለው።

አገልግሎቱ ስለእርስዎ ያለው የግል መረጃ ትክክል ካልሆነ ወይም ማዘመን የሚያስፈልገው ከሆነ፣ ወይም አገልግሎቱ ማንኛውንም የግል መረጃ እንዲሰርዝ ወይም አገልግሎቱ እርስዎን የማግኘት ዘዴውን እንዲቀይር ከፈለጉ፣ እባክዎን ጥያቄዎን በኢሜል ይላኩ።

ያግኙን