ስለ ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ስለ ደሬክ ፕሪንስ ሚኒስትሪ እና ስለ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርታችን ለሚነሱ የተለመዱ ጥያቄዎች መልስ ያግኙ።

የዴሪክ ፕሪንስ አገልግሎት ምንድን ነው?

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ መጽሐፍ ቅዱስን በማስተማርና አማኞች በእግዚአብሔር ቃል መሠረት እንዲኖሩ በማስታጠቅ ላይ የተሰማራ ዓለም አቀፍ ክርስቲያናዊ ድርጅት ነው። የዴሪክ ፕሪንስን ትምህርቶች በመጻሕፍት፣ በድምጽ፣ በቪዲዮ እና በዲጂታል ግብዓቶችን በማሰራጨት አሻራ መተዉን ይቀጥላል።

የእምነት መግለጫዎ ምንድን ነው?

ሙሉውን የእምነት መግለጫችንን ያንብቡ።

የእምነት መግለጫ

ዲፒኤም ምንድን ነው?

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ አንዳንድ ጊዜ ዲፒኤም በሚል ምዕጻረ-ቃል ይጠራል።

በሌሎች አገሮችስ እንዴት ነው የምትሠሩት?

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ በስድስት አህጉራት ላይ የተዘረጋ ከ45 በላይ አገር አቀፍ እና የተልዕኮ ቢሮዎች ያሉት ሲሆን የዴሪክን ትምህርቶች ከ100 በላይ በሆኑ ቋንቋዎች ተርጉሟል። ቡድኖቻችን የዴሪክን ትምህርቶች በሕትመት፣ በድምጽ፣ በቪዲዮና በሬዲዮ ይዘት እና አቀራረብ ተርጉመው ያሰራጫሉ።

ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን በተልዕኮ ስራዎቻችን በኩል ስለምናደርገው አስደናቂ ስራ የበለጠ ይወቁ።

ተልዕኮዎች

ዴሪክ ፕሪንስ ማን ነው?

ዴሪክ ፕሪንስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህርና ደራሲ ሲሆኑ ተደማጭነት ያለው አገልግሎታቸው በዓለም ዙሪያ ያሉ ክርስቲያኖችን ማነቃቃቱን ቀጥሏል። እጅግ ጥልቅ የሆነው የቅዱሳት መጻሕፍት ግንዛቤያቸውና የእግዚአብሔርን ቃል ለማካፈል ባላቸው ቁርጠኝነት ዘላቂ አሻረ ጥለዋል።

ስለ ደሬክ ፕሪንስ ሕይወት፣ ትምህርቶችና አስተዋጽኦዎች የበለጠ ለማወቅ እባክዎ የሕይወት ታሪኩን ይጎብኙ።

የሕይወት ታሪክ

ከዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ ጋር እንዴት መገናኘት እችላለሁ?

ለበለጠ መረጃ የእውቂያ ገጻችንን ይመልከቱ።

እውቂያ

የዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ አዳዲስ መረጃዎችን ለመቀበል እንዴት ሰብስክራይብ ማድረግ እችላለሁ?

ከዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ የሚወጡትን አዳዲስ ዜናዎችና መረጃዎች ለማግኘት በማኅበረሰባችን አዲስ መረጃዎች (updates) ላይ ሰብስክራይብ ያድርጉ።

ከእኛ ጋር ይገናኙ

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ ከሌሎች አገልግሎቶች ጋር ይተባበራል?

በዓለም ዙሪያ ካሉ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪ አገልግሎቶችና የሥነ-መለኮት ኮሌጆች ጋር በመተባበር መጋቢዎችንና ምእመናንን በዴሪክ ፕሪንስ ትምህርቶች እናስታጥቃለን። ዓላማችንም መጋቢዎች ሰፋ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ሃብት በመጠቀም የራሳቸውን ትክክለኛ አገልግሎት እንዲያዳብሩ መደገፍ ነው።

ኮንፈረንሶች ታዘጋጃላችሁ?

በአንዳንድ አገሮች የራሳችንን ኮንፈረንሶች እናዘጋጃለን፤ በሌሎች አገሮች ደግሞ ከአካባቢው አብያተ ክርስቲያናትና አገልግሎቶች ጋር እንተባበራለን። ለበለጠ መረጃ የአካባቢዎን የዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪዎች ቢሮ ያነጋግሩ።

አብያተ ክርስቲያናት ትተክላላችሁን?

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ ቤተክርስቲያናትን አይተክልም። ይልቁንም፣ልክ ዴሪክ ፕሪንስ እንዳደረገው ሁሉ፣ የአካባቢውን ክርስቲያን መሪዎች በወንጌላዊነት፣በደቀ መዝሙርነትና በቤተክርስቲያን እድገት እንደግፋለን። ተልእኳችን አሁንም ሳይለወጥ ይቀጥላል፤ ያልተደረሱትን መድረስና ያልተማሩትን ማስተማር ነው፣ይህንንም ብዙውን ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ ሃብቶችን በነጻ በማቅረብ እናደርጋለን።

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ የግል መረጃዬን እንዴት ያስተናግዳል እና ይጠብቃል?

በዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ፣ የግል መረጃዎትን ከፍተኛ ጥንቃቄና ታማኝነት በተሞላበት መንገድ ለመጠበቅ ቁርጠኞች ነን። የመረጃዎትን አጠቃቀምና ጥበቃ የሚመሩት ከሚገናኙበት ቢሮ የአካባቢ ግላዊነት መመሪያዎች እንዲሁም በአካባቢው ተፈጻሚ በሆኑ ሕጎችና ደንቦች ነው። ይህም መረጃዎ በኃላፊነት ስሜት እና አግባብ ካላቸው የሕግ መስፈርቶች ጋር በሚስማማ መልኩ ጥቅም ላይ እንዲውል ያረጋግጣል።

መረጃዎ እንዴት እንደሚሰበሰብ፣ እንደሚያገለግልና እንደሚጠበቅ የበለጠ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የግላዊነት መመሪያችንን ሙሉ በሙሉ እንዲያነቡ እናበረታታዎታለን።

የግላዊነት መመሪያ

የዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ ምን ዓይነት መርጃዎችን ያቀርባል?

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ግብዓቶችን እናቀርባለን፤ መጻሕፍትን፣ የድምጽ ትምህርቶችን፣ ቪዲዮዎችን፣ መንፈሳዊ ማስታወሻዎችንና የጥናት መምሪያዎችን ጨምሮ። ብዙዎቹ በነጻ ወይም በተመጣጣኝ ዋጋ ይገኛሉ።

ግብዓቶችን ይመልከቱ

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ኮርሶችን ያቀርባል?

አዎ፣ በአንዳንድ ቋንቋዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ኮርሶችን በማዘጋጀት አማኞችን በደንብ እናስተምራቸዋለን እንዲሁም ለእግዚአብሔር ቃል ያላቸውን ግንዛቤ እናሳድጋለን።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርቶች

የዴሪክ ፕሪንስ መጻሕፍት በሌሎች ቋንቋዎች ይገኛሉ?

አዎ! የዴሪክ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች በብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ። በተለየ ቋንቋ መጻሕፍትን የምትፈልጉ ከሆነ፣ የድረ-ገጻችንን መደብር ይመልከቱ ወይም ለዝርዝር መረጃ የአካባቢያችሁን የዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪዎች ቢሮ ያነጋግሩ። እነዚህ ግብዓቶች ለግል ጥናት ወይም ለማኅበረሰባችሁ ተደራሽነት በጣም ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።

እውቂያየቀጥታ የኢንተርኔት መስመር መደብር

የዴሪክ ፕሪንስን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ወደ ቋንቋዬ መተርጎም እችላለሁን?

ስለ ትርጉምና ህትመት ሂደታችን ዝርዝር መረጃ ለማግኘት በአቅራቢያዎ ወደሚገኘው ቢሮአችን ይደውሉ።

ትዕዛዜ አልደረሰም፤ አሁን ምን ላድርግ?

ለተጨማሪ እርዳታ በቀጥታ የኢንተርኔት መስመር ግዢው የተፈፀመበትን የአካባቢዎን ቢሮ ያግኙ።

እውቂያ

የዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስን እንዴት መደገፍ እችላለሁ?

በጸሎት፣ በገንዘብ እርዳታ ወይም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መደገፍ ይችላሉ። እንዴት መደገፍ እና መሳተፍ እንደሚችሉ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እባክዎን በአካባቢዎ ያለውን ቢሮ ያነጋግሩ።

ይለግሱ

ለዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ የሚደረጉ ልገሳዎች ከታክስ የሚቀነሱ ናቸውን?

በብዙ አገሮች፣ ለዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪ የሚደረጉ ልገሳዎች ከታክስ የሚቀነሱ ናቸው። ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃ እባክዎን በአካባቢዎ ያለውን ቢሮ ያነጋግሩ።