ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ታሪኮች

የዴሪክ ፕሪንስ ትምህርቶች በፈጠሩት መነቃቃት የተነሳ፤በመላው የዓለም ዙሪያ ከሚገኙ መጋቢዎች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችና አማኞች ዘወትር የምስክርነት ቃል እንቀበላለን። የዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪ እ.ኤ.አ ከ1971 ዓ.ም ጀምሮ ለምን የታመነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንጭ እንደሆነ እወቁ።

ሰዎች የሚሉት

የዴሪክ ፕሪንስ ትምህርቶችን መማር የጀመርኩት ከጥቂት ወራት በፊት ነበር። ለተማርኩት ነገር ሁሉ ምስጋናዬን መግለጽ አልችልም። አዲስ የመንፈሳዊ እውቀት ዓለም ተከፍቶልኛል። በየቀኑ አዳምጠዋለሁ፤ ለትምህርቶቹም ሰማያዊ አባታችንን አመሰግናለሁ።

ካርመን ኤም፣ ፈረንሳይ

የዴሪክ ፕሪንስ ስም በዓለም ዙሪያ ከንጹሕ አቋምና ከድፍረት ጋር ተመሳሳይ ሆኗል፤ ድፍረቱም አብዛኞቹ ሰባኪዎች ለማስተማር ይቅርና ለማሰብም የሚፈሩባቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሶች ለመናገር ነበር።

ጆን ሀጌ፣ የሀጌ ሚኒስትሪስ መስራች

ለበርካታ ዓመታት በዩቲዩብ ዴሪክ ፕሪንስን ሲያስተምር እከታተል ነበር። ትምህርቶቹ በጣም ጠንካራና አድስ ስለሆኑ ጠንካራ ትምህርት በሚጠፋበት በዚህ ዘመንም እንኳ ተጽዕኖ ማሳደሩን ቀጥሏል።

ሚነርቫ ኦ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

በዴሪክ ፕሪንስ ሕይወት ውስጥ የሠራው የእግዚአብሔር ኃይል፣ ጸሎቱና ታዛዥነቱ በዓለም ክስተቶች ላይ ለውጥ እንዴት እንዳመጣና በብዙ ሰዎች ሕይወት ውስጥ አዲስ መነቃቃት እንዳስገኘ እጅግ አደንቃለሁ። በዚህ ሰው ሕይወት ውስጥና በእርሱ በኩል ያለው የእግዚአብሔር ፍቅርና ዓላማ በጣም ይማርከኛል።

ፊል ኬጊ፣ ሽልማትን ያሸነፈ የሙዚቃ ባለሙያ እና ዘፋኝ

ከትምህርቶችዎ ብዙ ተምሬያለሁ።

ፓስተር ላዛሩስ ፒ፣ ዛምቢያ

ደሬክ ፕሪንስ ለሚሊዮኖች ፈር ቀዳጅ እና የእምነት አባት ነው። ልክ እንደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሞቱ በምድር ላይ ሕይወትን የሚያስቀጥል ዘር ሆኗል። ደሬክን በአካል በማግኘቴ ክብር ይሰማኛል፤ ከአገልግሎቱ በስተጀርባ ድንቅ ሰው እንዳለ በእውነት መናገር እችላለሁ።

ኪምበርሊ ዳንኤልስ፣ ኪምበርሊ ዳንኤልስ ሚኒስትሪስ ኢንተርናሽናል

የዴሪክ ፕሪንስን ትምህርቶች ስሰማ ቆይቻለሁ ሕይወቴንም ቀይሮታል። ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስን አመሰግናለሁ።

ሱዛና ቲ፣ አውስትራሊያ

ሁለት የአካዳሚ ሽልማቶችንና ሌሎች በርካታ እውቅናዎችን ብቀዳጅም፣ ኢየሱስን ማግኘቴና በሕይወቴ ውስጥ እርሱን ማኖሬ ከሁሉም በላይ እጅግ አስፈላጊው ነገር ነው። ዴሪክ ፕሪንስ ደግሞ ወዳጄና አስተማሪዬ በመሆኑ ብዙ ፍቅር፣ ደስታና ሰላም አግኝቻለሁ። እስከ ዛሬ ድረስ በወርሃዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቼ ዴሪክን እጠቅሳለሁ።

አል ካሻ፣ የአካዳሚ ሽልማት አሸናፊ አቀናባሪና የዜማ ደራሲ

ሕይወቴ በዴሪክ ፕሪንስ ትምህርቶች ተለውጧል።

ሚሪያም ጂ፣ ዩናይትድ ኪንግደም

በሕይወት ዘመናቸውና ተጽዕኖ ፈጣሪ በነበሩባቸው ዓመታት ሁሉ የዴሪክ ፕሪንስ አመራር እውነተኛ የሐዋርያት መንፈስ ያለበት በመሆኑ፣ በትምህርትና በምክር ጽሑፎቻቸው ጠቃሚ ይዘትን፣ ጥልቅ ማስተዋልንና ቅዱስ መንፈስን ጥለውልን አልፈዋል።

ጃክ ደብሊው ሃይፎርድ፣ የአለም አቀፍ የፎርስኩዌር ጎስፔል ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት እና የኪንግስ ኮሌጅ እና ሴሚናሪ ቻንስለር

በዴሪክ ፕሪንስ አገልግሎት በረከትንና ብርታትን ማግኘቴን እቀጥላለሁ! የዴሪክን ጥልቅ ትምህርቶች በቀላሉ ተደራሽ ስላደረጋችሁልኝ አመሰግናለሁ።

ሊን ሲ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ዴሪክ ፕሪንስ የነፃ መውጣት አገልግሎት ጀነራል ነበሩ፤ ከዘመኑ እጅግ ቀድመው እንደነበር ምንም ጥርጥር የለውም። ሞተው እያሉ ግን አሁንም ይናገራሉ፤ አሜን።

ግሬግ ሎክ፤ የግሎባል ቪዥን ባይብል ቤተክርስቲያን መስራች

ይህንን አገልግሎት እወደዋለሁ። ከጠላት መዳፍ ነፃ ወጥቻለሁ።

ፓትሪስ ኤ፣ ትሪኒዳድ እና ቶባጎ

የእምነት አባቶች የሚታወቁት በቆፈሩት መንፈሳዊ የእረፍት ጕድጓዶችና በሠሩት የመሥዋዕት መሠዊያዎች ነው። በጥንት ዘመን እንደነበረው ሁሉ ዛሬም እንዲሁ ነው። “ለክርስቲያናዊ ሕይወት መሠረታዊ እውነቶች” የተሰኘው መጽሐፍ በትውልዳችን አንድ የእምነት አባት እንደተገለጠ የሚያሳይ ማስረጃ ነው። የዚህ መጽሐፍ እውነቶች የተቆፈሩት እጅግ በጣም በመንፈሳዊ ቅንዓት፣ በጥንታዊ ምሁርነትና ሕይወትን በሚለውጥ መገለጥ በተሞላ ሰው ስለሆነ፣ ለዚህ ለተቸገረ ዘመን ጕድጓድና መሠዊያ ሆነዋል። እግዚአብሔር እንደ ዴሪክ ፕሪንስ ያሉ ብዙ ኃያላን ወጣቶችን ያስነሣልን።

ስቴፈን ማንስፊልድ፣ “የዴሪክ ፕሪንስ - የሕይወት ታሪክ” ጸሐፊ።

በዩቲዩብ ላይ የዴሪክ ፕሪንስን ትምህርት በአጋጣሚ አገኘሁ። በዓለም “በአጋጣሚ” እንላለን፤ ነገር ግን ይህ አጋጣሚ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ይህ ወደ እውነት ሁሉ የመራኝና ያስተማረኝ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ አምናለሁ። ይህ የሆነው ከአንድ ወር ገደማ በፊት ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየቀኑ እየተከታተልኩ ነው።

ሊሳ ጄ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ዓለም የዴሪክ ፕሪንስ ዕዳ እንዳለባት መናገር ማጋነን አይሆንም። ሕይወቱና ጥሎ ያለፈው አሻራው አህጉራትንና ትውልዶችን ተሻግሯል። ልዩ የሆኑ ጽሑፎቹ መንፈሳዊና አንዳንዴም ውስብስብ የሆኑትን ይይዛሉ፤በጸጋና [በግል] ተሞክሮ አማካይነት፤ [ዴሪክ] መንፈሳዊውን ግልጽ ያደርጋሉ፤ውስብስቡንም ይተነትናሉ። በራስ አገዝ መጻሕፍት፣በሐሰተኛ የሥነ ልቦና ትምህርትና በሰው አዕምሮ በተፈጠረ-ሥነ ምግባር በተሞላ ዓለም ውስጥ፣ በመረጃ ባህር ውስጥ እንዳንሰጥም እና በጥበብ እጦት እንዳንጠፋ የሚጠብቀን ቦታና ድምፅ ፈጥሯል። ጉዟቸውን ከዴሪክ ፕሪንስ አገልግሎት ጋር የሚጀምሩ ወይም የሚያስቀጥሉ ሁልጊዜ ይጠቀማሉ። በሐዋርያት ትምህርት ጸንታችሁ ከፊታችሁ ያለውን ሩጫ እንድትሮጡ ብቻ ሳይሆን ድል እንድታደርጉ እመኛለሁ።

ሚካኤል ፒትስ፣ ኮርነርስቶን ግሎባል ኔትዎርክ

በእውነት በዴሪክ ፕሪንስ አገልግሎት ተባርኬያለሁ። ትምህርቶቻችሁ ግልጽ ናቸው እናም ዘወትር የማዳምጥ ተከታይ ነኝ።

ዳሪል ኤል፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ዴሪክ ፕሪንስ በመቅደሳችን ሲያስተምር እናስታውሳለን። ይህንን የተወደደ የእግዚአብሔር ሰው ማስተናገድ ትልቅ ክብር ነበር።

የቀርሜሎስ ማኅበር

የዴረክ ፕሪንስን ስብከቶች ያገኘሁት በኮሮና ወረርሺኝ ሁሉ ነገር በተዘጋበት ጊዜ ነበር፤ሳዳምጠው ሰላምና ደስታ ይሰማኝ ነበር።

ሜይንግ፣ ማሌዥያ

ደካሞችን መርዳትና ለጠፉት ነፍሳት መጨነቅ ሁልጊዜም የዴሪክ ልብ ትኩረት ነበር።

ባሪ ሴጋል፣ የእስራኤል ራዕይ ፕሬዝዳንት እና ተባባሪ መስራች

ጥምቀት የወሰድኩት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሳለሁ ነበር፤በክርስትና ውስጥ ብዙ ተሳትፌ ነበር፤ ነገር ግን የክርስቶስ በመስቀል ላይ የሰራው ሥራ ለእኔ እንደሆነ አላውቅም ነበር። ኢየሱስ ለሌሎች እንጂ ለእኔ እንደማያስፈልገኝ አስብ ነበር። በኃጢአት ሕይወት ውስጥ ኖሬያለሁ። ከብዙ ዓመታት በኋላ ባዶ በሆነው ሕይወቴ ተሰላችቼ ጠንካራ አቅጣጫ እፈልግ ነበር። የማገኛቸውን ሁሉንም አነቃቂ ቪዲዮዎች ተመለከትኩ፤ ነገር ግን በውስጤ ዘላቂ ሰላም ላገኝ አልቻልኩም። ከተወሰነ ጊዜ ፍለጋ በኋላ እግዚአብሔርን በእውነት ለማግኘት ቆረጥኩ። አንድ ቀን ማታ በመኝታ ክፍሌ ውስጥ ተንበርክኬ እግዚአብሔርን ይቅር እንዲለኝ ጸለይኩኝ፤ እና መጽሐፍ ቅዱስን እንደገና ማንበብ ጀመርኩ። እግዚአብሔር ወደ ሮሜ 10፥9-10 መራኝ እና ለመቀበል እምነት ሰጠኝ። በመጨረሻም ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ለእኔ ያደረገውን አወቅሁ። እግዚአብሔር ይመስገን! በዩቲዩብ ቻናላችሁ አማካኝነት እምነቴን የጨመሩ ብዙ ትምህርቶችን አግኝቻለሁ፤ እናም ከክርስቶስ ጋር ለሚኖርኝ የሕይወት ጉዞ በጣም በተግባር የሚሰሩ ናቸው።

ሳሙኤል ዘድ፣ ታይዋን

ደሪክ ፕሪንስን በአክብሮትና በፍቅር እናስታውሰዋለን…

አሊሰን ኢስትዉድ፣ የዩኬ ብሔራዊ ዳይሬክተር፣ ኤቤኔዘር ኦፕሬሽን ኤክሶደስ

የዴሪክ ፕሪንስን ትምህርት ከሰማሁ በኋላ ሕይወቴ መቼም ተመሳሳይ አይሆንም። ሁለት ወር ሆኖኛል፤ በአኗኗሬ፣ በንግግሬና በአስተሳሰቤ ሙሉ በሙሉ የተለወጥኩኝ ሆኛለሁ። ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን! አመሰግናለሁ።

ሻውንዳ ጄ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የዴሪክ ለአባትነት ያለው መሻት ለክርስቶስ አካል የሆነ ሕያው አሻራ እና ሌሎች መሪዎች ሊከተሉት የሚገባ ምሳሌ ጭምር ነው።

ቼሪል ዊልኮክስ፣ የክርስቲያን ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ

ዴሪክ ፕሪንስ አስተማሪዬ ነው። በየቀኑ ከእርሱ እማራለሁ። በሕይወቴ ውስጥ በረከት ሆኖልኛል፤ ለዚህም ጌታችንን አመሰግናለሁ። አመሰግናለሁ!

ካርመን አር ኤም፣ ፈረንሳይ

ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ በክርስቲያናዊ አተያይ መንፈሳዊ ጦርነትንና መንፈሳዊውን ዓለም በማስተማር ረገድ ግንባር ቀደም ኃይል ሆኖ ቆይቷል። በዓለም ዙሪያ 45 ቢሮዎች ያሉት ይህ አገልግሎት ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ዓለም አቀፍ እውቅና፣ ተደራሽነትና ተጽዕኖ አሳድሯል።

የአር ኤም አይ ሚዲያ

ላለፉት ዓመታት ለዓለም ላደረጋችሁት የማያወላውል አገልግሎት አመሰግናለሁ። ባለፈው ዓመት አብዛኛውን ክፍል የዴሪክ ፕሪንስን ትምህርቶች እያዳመጥኩ ነበር። እንዴት ያለ መነቃቃት ነው።"

ዳንኤል፣ ዩናይትድ ኪንግደም

ከጥቂት ዓመታት በፊት የእግዚአብሔርን ቃል ሊያስተምረኝ የሚችል ሰው በጣም እፈልግ ነበር። እስከዚያ ጊዜ ድረስ አላገኘሁም ነበር፤ እውቀቴም በራሴ ከማንበብ ብቻ የመጣ ነበር። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን እየፈለግኩ እና ዩቲዩብን እየተመለከትኩ ሳለ የዴሪክ ፕሪንስን ትምህርት አገኘሁ። በጣም ተማረክሁ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቪዲዮዎቹን በየቀኑ እመለከታለሁ።

ብሩኖ ኤስ፣ ፖርቱጋል

ደሬክ ፕሪንስ በትምህርታቸው ዓይኔን ከፈቱልኝ እንዲሁም የምከተለውን ምሳሌ አስቀመጡልኝ።

ሉሲንዳ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

እኔና ባለቤቴ የዴሪክን ትምህርቶች በዩቲዩብ ላይ አግኝተን መንፈሳዊ ጦርነትን በትክክል እንድንረዳ ረድቶናል። አሁን ነፃ ወጥተናል እናም ከኢየሱስ ጋር በእምነት መመላለሳችንን እንቀጥላለን።

ፒዬትሮ ፒ፣ ስዊዘርላንድ

ለዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። በትክክለኛው ጊዜ በትክክለኛው ቦታ ላይ ናችሁ።

ቻርለስ ኤም፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ከሂንዱ ቤተሰብ የተወለድኩ ብሆንም ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስን ጌታና አዳኜ አድርጌ ተቀብያለሁ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በዩቲዩብ ዴሪክ ፕሪንስን አግኝቼ ከድብርት ተፈውሻለሁ። ብዙ ነገር ተምሬያለሁ እና (ከብዙ ፍለጋ በኋላ) አስተማማኝ የመጽሐፍ ቅዱስ መምህር አግኝቻለሁ። የእግዚአብሔርን ቃልና ወንጌል በመላው ዓለም በማሰራጨታችሁ ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪዎች በጣም አመሰግናለሁ።

ሽሬያስ ጄ፣ ህንድ

ዛሬ የዴሪክ ፕሪንስን መልእክት ለመጀመሪያ ጊዜ ተመለከትኩኝ። በጣም አነቃቂ ነበር። አመሰግናለሁ።

ቴሬዛ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

በዴሪክ ፕሪንስ ትምህርቶች በእውነት ተባርኬያለሁ።

አናማ ኪው፤ህንድ

ስለ ዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪዎች እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። እንዲህ ያለ ጥልቅና ወሳኝ ትምህርት ማግኘታችን በረከት ነው።

አን ኤም ፒ፣ ዩኤስኤ

ከጥቂት ጊዜ በፊት መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እሞክር ነበር ግን የነበረኝ የኪንግ ጀምስ ቨርዥን ሰለሆነ አልገባኝም ነበር። ሌሎች ትርጉሞች እንዳሉ አላውቅም ነበር። በጣም አላዋቂ ነበርኩ። ስለዚህ ወደ አንድ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ሞከርኩ ምክንያቱም እዚያ በእርግጥ እማራለሁ እነርሱም ሊያስረዱኝ ይችላሉ ብዬ አስብ ነበር። ወደ ብዙዎች ብሄድም በመጨረሻ ተስፋ ቆረጬ ነበር። በዙሪያዬ ያለ ማንም ሰው መንገዱን ሊያሳየኝ አልቻለም። ስለዚህ ተውኩት! በቅርቡ ዩቲዩብ ላይ ቪዲዮ እያየሁ ሳለ በድንገት የዴሪክ ፕሪንስን ቪዲዮ አገኘሁ። አሁን ሱሰኛ ሆኛለሁ! እሱ የምፈልገው አይነት ሰው ነበር። ቪዲዮዎቹ አሁንም ድረስ መኖራቸው እና ወደ ሌሎች ቋንቋዎች መተርጎማቸው በጣም ያስደስተኛል። ብዙ እየተማርኩ ነው! ቪዲዮዎቹን በየቀኑ እመለከታለሁ።

ቤሊሳ ጂ፣ አሜሪካ

በዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪ መልእክቶች እጅግ ተበረታትቻለሁ። የእግዚአብሔርን ቃል ለመማርና በቤተሰባችን ላይ በረከት ለማምጣት ያለኝ ጉጉት እየጨመረ መጥቷል። ላዘጋጃችሁት ሀብቶች ሁሉ አመሰግናለሁ።

ፒሊ ቢ፣ ሕንድ

የዴሪክ ፕሪንስ ትምህርቶች ሕይወቴን ቀይረውታል። አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ስለ መንፈሳዊው ዓለም በግልጽ አውቄ እኖራለሁ። ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ይህን አዲስ ጉዞ በመጀመሬ በጣም ተደስቻለሁ። ስለ እርግማንና በረከት መማሬ በእግዚአብሔር የታዘዘ ነበር። የዴሪክ ፕሪንስን የቪዲዮ መልእክቶች በኢንተርኔት ስመለከት እንኳን በክፍሌ ውስጥ ኃይለኛ የእግዚአብሔር መገኘት ይሰማኛል። እውነተኛ ነቢይና የእግዚአብሔር ሰው ነው። በሰማይ ሰላምታ ላቀርብለትና ላመሰግነው እናፍቃለሁ!

ሱዚ ግሬስ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ

ዴሪክ ፕሪንስን ጥልቅ ስለሆነው ትምህርቱ አመሰግነዋለሁ! ፍቅሩ፣ትዕግሥቱና መሰጠቱ ከጅምሩ በጣም ግልጽ ነበር! ብዙ ነገር አስተምሮኛል! ከምወዳቸውና ዘወትር ከማዳምጣቸው ሰባኪዎች አንዱ ነው! እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ተናግሮ ዓይኖቼ ለእውነት እንዲከፈቱ ረድቶኛል!

ኤልሳቤጥ፣ ካናዳ

ዴሪክ ልዑል