ደቀ መዝሙርነትን አበርክቱበት
ውርስ ለመተው ሀብታም መሆን አይጠበቅባችሁም፤ በቅድሚያ ለቤተሰቦቻችሁ ማቅረብ እንደምትፈልጉም እንረዳለን። ነገር ግን የምታበረክቱት ውርስ ምንም ያህል መጠን ቢኖረው እንደሚወደድና በእጃችንም በዓለም ዙሪያ ላሉ ብዙ ክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት ፍሬ እንደሚያፈራ እርግጠኛ ሁኑ። የስጦታችሁ ዋጋ ምንም ይሁን ምን፣ ለሚያስፈልገው ሰው ትልቅ እገዛ ይሆናል።
የዴሪክ ፕሪንስ ትምህርት ሕይወቴን መቼም በማልገምተው መንገድ ለውጦታል። ትልቁ ምኞቴ የወደፊቱ ትውልዶች የዴሪክን ሕይወት የሚለውጥ፤ተጸዕኖ ፈጣሪ የሆነ የቃሉን ኃይል የመለማመድ እድል እንዲያገኙ ነው። ለዚህም ነው ለዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪ ውርስ ለመተው የመረጥኩት። ይህ ስጦታ የዴሪክን ትምህርት ሕያው እንዲሆን፣ ወደ ሰማይ ከሄድን በኋላም እንኳ ለዓመታት የሰዎችን ሕይወት መንካቱን ይቀጥል ዘንድ እንደሚያግዝ አውቃለሁ።
ሕይወትን የሚለውጥ የእግዚአብሔር ቃል ኃይል ወደ ሕይወታቸው፣ ወደ ቤተክርስቲያናቸው እና ወደ አካባቢያቸው ማኅበረሰብ እንዲያሰራጩ የሚያስችላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤መንፈሳዊ ረሃብ ላላቸው ክርስቲያኖች እንዲያገኙ የእርስዎ የውርስ ስጦታ ያስችላል።
የውርስ ስጦታዎ ሕይወትን የሚለውጠው እንዴት ነው?
- የእርስዎ የውርስ ስጦታ የዴሪክን ትምህርት በዓለም ዙሪያ ላሉ አዳዲስ የክርስቲያን ትውልዶች በነፃ ተደራሽ ያደርገዋል።
- የእርስዎ ውርስ ስጦታ የዴሪክ ትምህርት በአዳዲስ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ታትሞ በየትኛውም ቦታ ያሉ አማኞችን ሊያበረታ ይችላል።
- የእርስዎ ውርስ ስጦታ ዲጂታል በሆነ መንገድ ደቀ መዝሙር የማፍራት ሥራን እና የወንጌል ስርጭት ቁሳቁሶችን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችንና ግብዓቶችን በማቅረብ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
- የእርስዎ የውርስ ስጦታ ለወደፊቱ መጋቢዎችን፣የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ተማሪዎች እና ወንጌላውያን የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት እንዲቆፍሩ እና ወደ ክርስቶስ የመጡትን ደግሞ ደቀመዛሙርት እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
በውርስ ኑዛዜዎ እንዴት እንደሚያካትቱን
የዴሪክ ፕሪንስ ሚኒስትሪስ
የተመዘገበ የበጎ አድራጎት ድርጅት።
ቀድሞውኑ ኑዛዜ ካለዎት፣ የኑዛዜ ቃል ቅጻችንን በመጠቀም ቀላል ለውጥ ማድረግ ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ያግኙን። ሙሉ የሕግ ምክር ለማግኘት ጠበቃ ማማከርን እንመክራለን።
ያግኙን