ለዘላለም ኑሩ

ዴሪክ ፕሪንስ
Published: 1970
Last Updated: ኦክቶበር 2026
Read Time: 2
ተለዋዋጭ የሆነው ዓለም ዘላቂ ዋስትና ሊሰጥ አይችልም። በዚህ የዕለት ተዕለት መንፈሳዊ ትምህርት ውስጥ፣1ኛ ዮሐንስ 2:17 የእግዚአብሔር የማይለወጥ ፈቃድ ለሚያደርጉት ሁሉ ጽኑ መሠረት እንደሆነ ይገልጻል።
ዴሪክ ፕሪንስ ነኝ፤ ከቃሉ ለእናንተ የሚሆን መልዕክት ይዤላችሁ ቀርቤአለሁ።
ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። 1ኛ ዮሐንስ 2:17
እኛ የምንኖረው በጣም በማይጸና እና ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ ነው። የምናየው ማንኛውም ነገር ለዘላለም የሚጸና አይደለም። በዚህ ዓለም ውስጥ በጊዜያዊ ነገሮችና በሥጋ ምኞት ውስጥ የተዘፈቁ ሰዎች መሻቶች፣ፍላጎቶች እና ምኞቶች ሁሉ ያልፋሉ። በዓለም ውስጥ የሚሠሩ ኃይሎች አሉ - ከእኛ ይልቅ እጅግ ኃያላን የሆኑ፣እኛ ልንቆጣጠራቸው የማንችላቸው መንፈሳዊና ቁሳዊ ኃይሎች አሉ። እኛ ልክ በወንዝ ላይ ተንሳፍፎ እንደሚወሰድ አንዲት ትንሽ ቅንጣት ነን።
ዘላቂነትን ለማግኘት የሚያስችል መንገድ አለን? ዋስትናን ለማግኘት የሚያስችል መንገድ አለን? አዎ፣ነገሩ ቀላል ነው። እነዚህ ቃላት መልሱን ይዘዋል፦ “የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።” በመጨረሻም የእግዚአብሔር ፈቃድ ጸንቶ ይቆማል። ሌላው ነገር ሁሉ ሲፈርስና ሲወገድ፣ ጊዜያዊና ዋስትና የሌለው ሲሆን፣ ተስፋ ሲያስቆርጠንና ምናልባትም ሲያታልለን፣ ጸንቶ የሚቆም አንድ ነገር አለ፤እርሱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
እግዚአብሔር በሁሉ ላይ ስልጣን አለው፤ እርሱ ኃያል ነው። ራሳችሁን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር ካቆራኙና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግ የሕይወታችሁ ዓላማ ካደረጋችሁ፣ ልክ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጠንካራ፣ የጸናችሁ እና ደህንነታችሁ የተጠበቀ ትሆናላችሁ። ሁኔታዎች ይለዋወጣሉ፣ ዓለምም ትለወጣለች፤ የእግዚአብሔር ፈቃድ ግን ጸንቶ፣ ዘላቂና የማይሸነፍ ሆኖ ለዘለዓለም ይኖራል፤ እናም ለማድረግ ከቆረጣችሁ ልክ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መሆን ትችላላችሁ።

ኮድ: WD-WFTW-006-AMH









